የተቋሙ ስልጣን ፤ ተግባርና ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
የኢንተርኘራይዞችንና የሥራ ፈላጊዎችን የስራ ገበያ መረጃ ይመዘግባል፤ መረጃ ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
ለሥራ ፈላጊዎችና ለኢንተርፕራይዞች በሥራ ዕድል ፈጠራ ስትራቴጂ፣ አሰራርና የድጋፍ ማዕቀፎች ላይ ግንዛቤ ይፈጥራል፤ አፈፃፀሙን እየተከታተለ ድጋፍ ያደርጋል፤
የኢንተርኘራይዞችን የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ያቋቁማል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎችን በንግድ ህጉ እና አግባብ ባለው ሌላ ህግ መሰረት ያደራጃል፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
በኢንተርኘራይዝ ለተሰማሩ አንቀሳቃሾችና አምራቾች የሙያ ማበልፀጊያ ስልጠናዎች እና አውደ ርዕዮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞችን ለማሳደግ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከጥናትና ምርምር ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ይሰራል፣
ኢንተርኘራይዞችን የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ መረጣ፣ የድርድር፣ የግንባታ፣ የኮሚሺኒንግ ድጋፍ ይሰጣል፤ ውጤቱንም ይገመግማል፤
ለኢንተርኘራይዞችን የመረጃና የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፤
የኢንተርኘራይዞችን የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የደረጃ እና የጥራት ሰርቲፊኬሽን እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞችን ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ፤ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛና ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞችን ተወዳዳሪ ለማድረግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የማበረታቻ፣ የዕውቅና እና ሽልማት ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
የኢንተርኘራይዞችን በዘርፍ ማህበራት ያደራጃል፤ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ በህግ መሰረት ይሰጣል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤ ይሰርዛል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች እና የግል የስራ ሁኔታ ቁጥጥር አገልግሎት አቅራቢዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠት፤
ስለውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችን መስራት፤
ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
- የሥራ ስምሪት በማስፋፋት የስራ ዕድል መፍጠር
- በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ ማድረግ
- ምቹ የሥራ ቦታና አካባቢ መፍጠር